am_tn/isa/30/25.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ለይሁዳ ሰዎች መናገሩን ቀጥሏል፡፡

በረጅሙ ተራራ ሁሉ … ሰባት ቀን የፀሐይ ብርሃን

ኢሳይያስ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከታደገ በኋላ የሚኖረውን ምናባዊ ሁኔታ ይገልጻል፡፡ የቋንቋ አጠቃቀሙ ግነታዊ ነው፤ ይህንን ኢሳያያስ እንደ ገለጸው እንደዚያው መተርጎም ይኖርብሃል፡፡

በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ

"እግዚአብሔር ጠላቶቻችሁን በጨረሰና ትላልቅ ግንቦቻቸው እንዲወድቁ ባደረገ ጊዜ'

በዚያን ቀን

"በዚያን ጊዜ'

የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን የፀሐይ ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል

"ሰባት ፀሐዮች እንደሚያበሩት ፀሐይ ታበራለች' ወይም "ፀሐይ በተለምዶ በሰባት ቀን የምትሰጠውን ያህል ብዙ ብርሃን በአንድ ቀን ትሰጣለች'

እግዚአብሔር የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፣ የቆሰለውንም በፈወሰ ዕለት

የእግዚአብሔር ሕዝቡን ማጽናናትና መከራቸው እንዲያበቃ ማድረጉ ቁስላቸውን በፋሻ እንዳሰረላቸው ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)