am_tn/isa/30/20.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ለይሁዳ ሕዝብ መናገሩን ይቀጥላል፡፡

የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ

በዚህ ስፍራ "እንጀራ' እና "ውኃ' በጣም ድሀ የሆነ ሰው ምግብ ነው፡፡ ሐረጉ እንዳለ የመከራን ጊዜና የሕዝቡን ድህነት ይወክላል፡፡ (ምትክ ስም ተመልከት)

አስተማሪህን

ይህ እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡

አስተማሪህን በገዛ ዓይኖችህ ታያለህ

በዚህ ስፍራ "ዓይኖች' የሰወን ሁለንተና ይወክላሉ፡፡ አት፡- "አንተ ራስህ አስተማሪህን ታያለህ' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)

ጆሮችህ ይሰማሉ

በዚህ ስፍራ "ጆሮች' የሚለው የሰውን ሁለንተና ይወክላሉ፡፡ አት፡- "ትሰማለህ' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)

በኋላህ የሚለውን ቃል

ከኋላህ እንዲህ በማለት የሚናገረውን

መንገዱ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ

ሕዝቡ እንዴት መኖር እንዳለባቸው እግዚአብሔር ያለው ፍላጎት በላዩ እንደሚከድበት መንገድ ወይም ጎዳና ተደርጎ ተነገሮአል፡፡ ለእግዚአብሔር መታዘዝ አንድ ሰው በእግዚአብሔር መንገድ እንደሄደ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ወደ ቀኝ ፈቀቅ ስትል ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ ስትል

ለእግዚአብሔር አለመታዘዝ ከእግዚአብሔር መንግድ ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ ፈቀቅ እንደ ማለት ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)