am_tn/isa/30/15.md

1.7 KiB

የእስራኤል ቅዱስ

ይህን ስም በኢሳይያስ 1፡4 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ

ንስሐ መግባት በአካል ወደ እግዚአብሔር እንደ መመለስ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ንስሐ ከገባችሁና እንደምጠነቀቅላቸሁ በማወቅ ካረፋችሁ ከጠላቶቻችሁ አድናችኋለሁ፡፡' (ስዕላዊ ንግግር እና አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

በማረፍ

እግዚአብሔር እንደሚጠነቀቅላቸው ከማመን የተነሳ ሕዝቡ ማረፉን ያመለክታል፡፡ (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል

ጸጥታ በዚህ ስፍራ ተጨናቂና ስጉ አለመሆንን ያመለክታል፡፡ በእግዚአብሔር ከመታመናቸው የተነሣ የማይጨነቁ መሆናቸውን ያመለክታል፡፡ አት፡- ጸጥ ካላችሁና በእኔ ከታመናችሁ ትበረታላችሁ (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን

በግልጽ እነዚህ የይሁዳ ሰዎች ከግብጻውያን የወሰዱአቸው ፈረሶች ናቸው፡፡ (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)