am_tn/isa/30/14.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ እግዚአብሔር የይሁዳን ሕዝብ እንዴት እንደሚያጠፋ ይገልጻል፡፡ (ኢሳይያስ 30፡ 12-13 ተመልከት)

እርሱን ይሰብረዋል

በዚህ ስፍራ እርሱን የሚለው ሊወድቅ ያለውን የቅጥሩን ጎን ያመለክታል፡፡ የቅጥሩ ጎን የይሁዳን ሕዝብና በኢሳይያስ 30፡ 12-13 የተጠቀሰውን ኃጢአታቸውን የሚወክል ስዕላዊ ንግግር ነው፡፡ (ስዕላ ንግግር ተመልከትሰ)

የሸክላ እቃ እንደሚሰበር

ይህ ዘይቤአዊ ንግግር ወደ መሬት እንደ ወደቀ የሸክላ ማሰሮ የቅጥሩ ጎን ፈጥኖ እና ሙሉ ለሙሉ ይሰበራል ማለት ነው፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)

ሸክላ ሠሪ

ሸክላ ሠሪ ከሸክላ አፈር ገንቦና ማሰሮ የሚሠራ ሰው ነው፡፡

አይገኝም

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ማንም ሊያገኘው አይችልም' ወይም "አይኖርም' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

የሚዛቅበት ስባሪ

"ለመዛቅ በቂ የሆነ ስባሪ'

እሳት ከምድጃ

"እሳት' የሚለው ቃል በዚህ ስፍራ አመድን ያመልክታል፡፡ አት፡- "አመድን ከእሳት ማንደጃ' (ምትክ ስም ተመልከት)