am_tn/isa/30/12.md

2.4 KiB

የእስራኤል ቅዱስ

ይህን ስም በኢሳይያስ 1፡4 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

ይህን ቃል አቃልላችኋል

ይህን መልእክት አቃልላችኋል

በግፍና በማታለል ታምናችኋል በእርሱም ተደግፋችኋል

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፤- 1) የይሁዳ መሪዎች ሌሎችን በመጨቆንና በማታለል በሚገዙ በግብጻውያን መሪዎች ታምነዋል ወይም 2) የይሁዳ መሪዎች ገንዘባቸውን ለመውሰድና ለሚደረግላቸው ጥበቃ ለግብጻውያን መሪዎች ክፍያ ለመላክ የገዛ ሕዝባቸውን ይጮቁኑና ያታልሉ ነበር፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመለከት)

በእርሱም ተደግፋችኋል

በዚህ ስፍራ "በእርሱ' የሚለው ግፍንና ማታለልን ያመለክታል፡፡ አት፡- "በእነርሱ ተደግፋችኋል' (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሦሥተኛ መደብ ተመልከት)

በእርሱም ላይ

በአንድ ነገር ላይ መታመን ወይም መደገፍ የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

ስለዚህ ይህ በደል እንደ ፈረሰ ጎን ይሆንባችኋል … በድንገት

ይህ ዘይቤአዊ ንግግር ከበደላቸው የተነሣ እግዚአብሔር የይሁዳን ሕዝብ በድንገት ያጠፋቸዋል የሚል ነው፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)

ለመውድቅ እንደ ቀረበ እንደ ፈረሰ ጎን

ይህ የተሰበረ የቅጥር ጎን አንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ አት፡- "ለመውደቅ እንደቀረበ የፈረሰ የቅጥር ጎን' (መቅረታቸው አሳቡን ከመረዳት ስለማያጓድሉ የተዘለሉ ተመልከት)

አወዳደቁም በድንገት እንደሚሆን

አወዳደቅ የሚለው የነገር ስም ወደቀ በሚል ማሰሪያ አንቀጽ እንዲገለጽ ይህ እንደገና ሊጻፍ ይችላል፡፡ አት፡- "በድንገት ይወድቃል' (የነገር ስም ተመልከት)

በድንገት፣ ፈጥኖ

እነዚህ አንድ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ቅጥሩ እንዴት ፈጥኖ እንደሚወድቅ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ (የሁለት ነገሮች ተመሳሳይነት)