am_tn/isa/30/06.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህ ክፍል የይሁዳን ሕዝብ በሚመለከት የእግዚአብሔርን አዋጅ ማቅረቡን ይቀጥላል

አዋጅ

"እግዚአብሔር ይህን ያውጃል'

እንስትና ተባት አንበሳ፣ እፉኝትም የሚበርር ቁጡ እባብ

ይህ እንደ እነዚህ ዓይነት እንስሳትን በአጠቃላይ ያመለክታል፡፡ አት፡- "እንስትና ተባት አንበሳ በሚያድሩበት ስፍራ፣ እንዲሁም እፉኝትና እባብ ባለበት' (አጠቃላይ ስማዊ ሐረጎች ተመልከት)

ቁጡ በራሪ እባብ

በዚህ ስፍራ "ቁጡ' የሚለው ቃል ምናልባት የእባቡን መርዛማ መናደፍ ያመለክታል፣ "በራሪ' የሚለው ቃልም ፈጣን እንቅስቃሴውን ያመለክታል፡፡ ይህንን በኢሳይያስ 14፡29 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

ኃብታቸውን ያግዛሉ

"የይሁዳ ሰዎች ኃብታቸውን ያግዛሉ'

እስካሁን የሚቀመጥ ረዓብ ብዬ ጠርቼዋለሁ

ስሙ ረዓብ ስለተባለ አስፈሪ የባሕር ፍጡር ታዋቂ የሆነ ታሪኮች አሉ፡፡ ረዓብ የሚለው ስም "ጥንካሬ' ወይም "እብሪት' ማለት ነው፡፡ አት፡- "ግብጽን ምንም የማያደርግ የሚጮኽ ጉረኛ ብዬ ጠርቼዋለሁ' (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)