am_tn/isa/30/03.md

1.7 KiB

አጠቃልይ መረጃ

እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ መናገሩን ይቀጥላል፡፡

ስለዚህ የፈርዖን ጥበቃ እፍረት በግብጽም ጥላ መሸሸግ ውርደት ይሆንባችኋል

"ጥበቃ'፣ "እፍረት' እና "ውርደት' የተሰኙት የነገር ስሞች እንደ ቅጽሎች ወይም ማሰሪያ አንቀጾች እንዲገለጹ ይህ እንደገና ሊጻፍ ይችላል፡፡ አት፡- "ፈርዖን ይጠብቀናል ስትሉ ስለታመናችሁ ታፍራላችሁ፣ በሰላም እንዲጠብቋችሁ በግብጻውያን ስለታመናችሁ ትዋረዳላችሁ' (የነገር ስሞች ተመልከት)

በግብጽ ጥላ መሸሸግ

ከጠላት ሠራዊት የሚደረገው የግብጻውያን ጥበቃ ጥላ አንድን ሰው ከሚያቃጥል የፀሐይ ሙቀት እንደሚጠብቅ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ልዑላኖቻቸው

በዚህ ስፍራ ልዑላን ማለት ሕጋዊ ባለሥልጣን ወይም አምባሰደር ማለት ነው፣ የግድ የንጉሥ ልጆች ማለት አይደለም፡፡

የእነርሱ … እነርሱ … እነሱ

እነዚህ ቃላት የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡

ዞአን … ሓኔስ

እነዚህ በግበጽ ሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ ከተሞች ናቸው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)

ወደ ሓኔስ ቢመጡ

በዚህ ስፍራ "መጣ' የሚለው "ሄደ' ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ (ሄደና መጣ ተመልከት)

ከሕዝቡ የተነሳ

"ከግብጽ ሕዝብ የተነሳ'