am_tn/isa/30/01.md

2.2 KiB

ዓመፀኞቹ ልጆች

እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ልጆቹ እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እያወጀ ያለውን ነገር እርግጠኝነት ለመግለጽ እግዚአብሔር በራሱ ስም ይናገራል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ያወጀው ይህ ነው' ወይም "እኔ፣ እግዚአብሔር ያወጅኩት ይህ ነው' (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሦሥተኛ መደብ ተመልከት)

እቅዶችን ያወጣሉ፣ ነገር ግን ከእኔ አይደለም

እቅዶች የሚለው የነገር ስም አቀደ በሚል ማሰሪያ አንቀጽ እንዲገለጽ ይህ እንደገና ሊጻፍ ይችላል፡፡ አት፡- "ነገሮችን ለማድረግ አቀዱ፣ ነገር ግን እንዲያደርጉ የምፈልገውን አልጠየቁኝም' (የነገር ስሞች ተመልከት)

ነገር ግን በመንፈሴ አይመሩም

ይህ በአደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ነገር ግን መንፈሴ አይመራቸውም' (አድራጊ ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

በኃጢአት ላይ ኃጢአት ይጨምራሉ

ኃጢአት በማድረግ መጽናት ኃጢአቶች አንዳቸው በአንዳቸው ላይ እንደሚከመሩ ቁሳ ቁሶች ተደርገው ተነግረዋል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ከፈርዖን ዘንድ ጥበቃ ፈለጉ

"ጥበቃ' የሚለው የነገር ስም "ጠበቀ' በሚለው ማሰሪያ አንቀጽ እንዲገለጽ ይህ እንደገና ሊጻፍ ይችላል፡፡ አት፡- "እንዲጠብቃቸው ፈርዖንን ጠየቁት' (የነገሮች ስም ተመልከት)

በግብጽ ጥላ ይሸሸጋሉ

ከጠላት ሠራዊት የሚደረገው የግብጻውያን ጥበቃ ጥላ አንድን ሰው ከሚያቃጥል የፀሐይ ሙቀት እንደሚጠብቅ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "በሰላም እንዲጠብቋቸው በግብጻውያን ይታመናሉ' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)