am_tn/isa/29/22.md

3.3 KiB

የያዕቆብ ቤት

በዚህ ስፍራ "ቤት' የሚለው ቤተሰብን ይወክላል፡፡ አት፡- "የያዕቆብ ትውልዶች' (ምትክ ስም ተመልከት)

አብርሃምን የተቤዠ

ይህ ምናልባት የሚያመለክተው እግዚአብሔር አብርሃምን ከትውልድ አገሩ የጠራበትንና ወደ ተስፋይቱ ምድር የላከበትን ጊዜ ነው፡፡ (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

ያዕቆብ ከእንግዲህ ወዲያ … ፊቱ … ልጆቹን ያያል

በዚህ ስፍራ "ያዕቆብ' የሚለው ትውልዶቹን ይወክላል፡፡ አት፡- "የያዕቆብ ትውልዶች ከእንግዲህ ወዲያ … ፊታቸው … ልጆቻቸውን ያያሉ' (ምትክ ስም ተመልከት)

ወይም ፊቱ አይለወጥም

ከእንግዲህ ወዲያ አይፈራም የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "ወይም አይፈሩም' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

ነገር ግን የእጆቼን ሥራ ልጆቹን ባየ ጊዜ

በዚህ ስፍር እጅ የሚለው የእግዚአብሔርን ኃይልና ሥራ ይወክላል፡፡ አት፡- "የሰጠኋቸውን ልጆችና ያደረግሁላቸውን ሁሉ ባየ ጊዜ' (ምትክ ቃል ተመልከት)

ስሜን ይቀድሳሉ

በዚህ ስፍራ "ስም' እግዚአብሔርን ይወክላል፡፡ አት፡- "ያከብሩኛል' (ምትክ ስም ተመልከት)

የያዕቆብን ቅዱስ ስም ይቀድሳሉ

በዚህ ስፍራ "ስም' እግዚአብሔርን ይወክላል፡፡ እግዚአብሔር ራሱን "የያዕቆብ ቅዱስ' ብሎ ይጠራል፡፡ አት፡- "የያዕቆብን ቅዱስ፣ እኔን ያከብሩኛል፡፡' (ምትክ ስምና አንደኛ፣ሁለተኛና ሦሥተኛ መደብ ተመልከት)

የእስራኤልንም አምላክ

እግዚአብሔር ራሱን "የእስራኤል አምላክ' ብሎ ይጠራል፡፡ አት፡- "እኔን፣ የእስራኤልን አምላክ' (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሦሥተኛ መደብ ተመልከት)

በመንፈስ የሳቱ

በዚህ ስፍራ "መንፈስ' የሚለው የሰውን ውስጣዊ ማንነት ይወክላል፡፡ አት፡- "በሚያስቡት የተሳሳቱ' ወይም "በዝንባሌአቸው የተሳሳቱ' (ምትክ ስም ተመልከት)

መረዳትን ያገኛሉ

የሚረዱት ምን እንደሆነ በማብራራት ይህ በይበልጥ ገልጽ ሊሆን ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔርንና ሕግጋቱን መረዳት ይጀምራሉ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

የሚያጉረመርሙ እውቀትን ይማራሉ

የሚማሩት እውቀት ምን እንደሆነ በማብራራት ይህ በይበልጥ ግልጽ ሊሆን ይችላል፡፡ አት፡ "የሚያጉረመርሙ እግዚአብሔር የሚያስተምራቸው እውነት እንደሆነ ማወቅ ይጀምራሉ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)