am_tn/isa/29/20.md

2.1 KiB

ጨካኞች ይጠፋሉና

"ጨካኞች' የሚለው ስማዊ ቅጽል፣ በቅጽልነት ሊቀመጥ ይችላል፡፡ አት፡- "ጨካኞች ሰዎች ይጠፋሉና' (ስማዊ ቅጽል ተመልከት)

ፌዘኞቹ ይጠፋሉና

"ፌዘኞች' የሚለው ስማዊ ቅጽል በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊተርጎም ይችላል፡፡ አት፡- "የሚያፌዙ ይጠፋሉና' ወይም "የሚያሾፉ ሰዎች ይጠፋሉና' (ስማዊ ቅጽል ተመልከት)

ክፉ ለማድረግ የሚወዱ ሁሉ ይጠፋሉ

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ክፉ ማድረግ የሚወዱትን ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

በቃል ሰውን በደለኛ የሚያደርጉ

ይህ በችሎት አንድን ሰው በመቃወም ምስክርነትን መስጠትን ያመለክታል፡፡ አት፡- "አንድን ሰው በመቃወም የሚመሰክርና በደለኛም የሚያደርገው' ወይም "አንዳች ስሕተት ፈጽሟል በሚል ችሎት ላይ ንጽሑን ሰው በደለኛ የሚያደርግ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

በበርም ላይ ፍትሕ ለሚፈልግ ወጥመድ የሚያኖሩ ጻድቁንም በባዶ ሐሰት እንዲሸማቀቅ የሚያደርጉ

መልካሙን ሰው ለማስቆም ክፉ ሰዎች የሚያደርጉት የትኛውም ነገር አዳኝ የሚያድነውን አጥምዶ እንደሚይዝ እንደዚያው ክፉ ሰዎች ወጥመድ እንደሚያጠምዱ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "ተገቢና ትክክል የሆነውን የሚያደርጉትን ለማስቆም ይጥራሉ ይዋሻሉም፡፡' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

በበር ላይ ፍትሕ ለሚፈልግ

የከተማይቱ በር ብዙውን ጊዜ የከተማይቱ መሪዎች ሕጋዊ ውሳኔዎችን የሚያስተላልፉበት ቦታ ነው፡፡