am_tn/isa/29/13.md

2.2 KiB

ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፣ በከንፈሮቹም ያከብረኛል

"አፍ' እና "ከንፈር' የሚሉት ቃላት ሕዝቡ የሚናገረውን ይወክላሉ፡፡ በዚህም ስፍራ አንድ ነገር መናገርን ነገር ግን በእውነታው የተባለውን የማይል ንግግርን ይወክላል፡፡ አት፡- "የኢየሩሳሌም ሰዎች በንግግር እኔን የሚያመልኩና የሚያከብሩ ያስመስላሉ' (ምትክ ስም ተመልከት)

ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው

በዚህ ስፍራ "ልብ' የሚለው የሰውን አሳብና ስሜት የሚወክል ምትክ ስም ነው፡፡ ለእግዚአብሔር በእውነት ያልተሰጠ ሕዝብ ልቡ ከእርሱ ርቆ እንደ ሄደ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "ነገር ግን በአሳቡ አያከብረኝም' ወይም "ነገር ግን በእውነት ለእኔ የተሰጠ አይደለም' (ምትክ ስም እና ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ያከብሩኛል

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ሰዎች እንዲያደርጉ የነገሯቸው ያ ስለሆነ ብቻ ያከብሩኛል' (አድረጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ስለዚህ፣ እይ፣ በዚህ ሕዝብ መካከል ድንቅ ነገር እንደገና አደርጋለሁ፣ በተዓምራት ላይ ተዓምራት

"ስለዚህ ተመልከትና እይ! ልታብራራቸው የማትችላቸውን አስደናቂና አስገራሚ ነገሮች በመካከልህ አደርጋለሁ'

የጥበበኞቻቸው ጥበብ ትጠፋለች፣ የአስተዋዮቻቸውም ማስተዋል ትሰወራለች

ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች አንድ ነገር ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር ያደረገውን ጠቢባን ሰዎች ሊረዱና ሊያብራሩ አለመቻላቸውን እግዚአብሔር መግለጡ ጥበባቸውና ማስተዋላቸው እንደጠፋ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (አጓዳኝነትና ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)