am_tn/isa/29/09.md

2.6 KiB

ራሳችሁ ተደነቁ፣ ተደነቁም

"ራሳችሁ' የሚለው ቃል በኢየሩሳልም የሚኖሩትን ሰዎች ያመልከታል፡፡ ለምን እንደሚደነቁ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አት፡- "እየነገርኳችሁ ባለው ነገር ተደነቁ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ እና የሁለት ነገሮች ተመሳሳይነት ተመልከት)

ራሳችሁን አሳውሩ እውሮችም ሁኑ

ሕዝቡ እግዚአብሔር የሚለውን ችላ ማለታቸው ራሳቸውን እንዳሳወሩ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "ለማሳያችሁ ነገር ቸልተኛና በመንፈስ እውር በመሆን ቀጥሉ' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

በወይን ጠጅ አይሁን እንጂ ስከሩ፤ በሚያሰክር መጠጥ አይሁን እንጂ ተንገድገዱ

ሕዝቡ ማስተዋል የጎደላቸውና እግዚአብሔር እያደረገ ያለው ነገር የማይረዱ መሆናቸው ሰካራሞች እንደሆኑ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "እንደ ሰካራም ሰው ማስተዋል የጎደላችሁ ሁኑ ነገር ግን ብዙ ወይንና የሚያሰክር መጠጥ ስለጠጣችሁ አይሁን፡፡' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

እግዚአብሔር የጥልቅ እንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል

በዚህ ስፍራ "የ… መንፈስ' ማለት የእንቅልፋምነት ባሕርይ ያለው መሆን ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡ እንዲተኛ ማድረጉ "መንፈሱ' በሕዝቡ ላይ የሚያፈስሰው ፈሳሽ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮል፡፡ "ጥልቅ እንቅልፍ' ማለት ሕዝቡ ማስተዋል የጎደለውና እግዚአብሔር እያደረገ ያለውን የማይረዳ ነው የሚል ትርጉም ያለው ስዕላዊ ንግግር ነው፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ዓይኖቻችሁን ከድኖታል፣ ነቢያቱን፣ ራሶቻችሁንም ሸፍኖታል፣ ባለራእዮችን

እግዚአብሔር ሕዝቡን ማስተዋል የጎደላቸውና እርሱ እየፈጸመው ያለውን የማይረዱ ማድረጉ ማየት እንዳይችሉ ዓይኖቻቸውን እንደከደነውና ራሶቻቸውን እንደሸፈነው ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "እንዲሁም እግዚአብሔር የነቢያቱን ዓይኖች ከድኖአል የባለራእዮቹንም ራሶች ሸፍኖአል' ((ስዕላዊ ንግግርተመልከት))