am_tn/isa/29/07.md

2.1 KiB

እንደ ሕልምና እንደ ሌሊት ራእይ ይሆናል

"የሌሊት ራእይ' የሚለው ሐረግ "ሕልም' ከሚለው ጋር ተመሣሣይ ነው፡፡ ሁለቱ ሐረጎች በዚያ እንዳልነበረ እንደ ወራሪው ሠራዊት ፈጥኖ እንደሚሆን አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ (የሁለት ነገሮች ተመሳሳይነት እና ዘይቤአዊ አነጋገር ተመልከት)

የሕዝቦች ሁሉ ብዛት

"ከሕዝቦች ሁሉ የሆነ ታላቅ ሠራዊት'

አርኤልን የሚዋጉ

"አርኤል' የሚለው ስም የኢየሩሳሌም ሌላ ስም ሲሆን፣ በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ይወክላል፡፡ "አርኤልን' በኢሳይያስ 29፡1 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ አት፡- "የአርኤልን ሰዎች የሚዋጉ' (ምትክ ስም ተመልከት)

ምሽጎችዋ፡፡ እርስዋን ለመጫን እርሷንና ምሽጎችዋን ይወጋሉ

"እርስዋ' የሚለው ቃል በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች የምትወክለውን አርኤልን ያመለክታል፡፡ አት፡- "ምሽጎቻቸው፡፡ የአርኤልን ከተማና መከላከያዎቿን ይወጋሉ ሕዝቡንም በታለቅ በመከራ ውስጥ እንዲገባ ያደርጋሉ፡፡' (ምትክ ስም ተመልከት)

የተራበ ሰው በሕልሙ እንደሚበላ ይሆናል … ጥሙ እንደማይረካ

እነዚህ ዘይቤአዊ ንግግሮች ጠላቶች ድል ቢጠብቁም እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዲያሸንፉ ስላልፈቀደላቸው አልተሳካላቸውም ማለት ነው፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)

እንዲሁ የጽዮንን ተራራ የሚወጉ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት ይሆናል

በዚህ ስፍራ የጽዮን ተራረ የሚለው በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ይወክላል፡፡ አት፡- "አዎን፣ በጽዮን ተራራ የሚኖሩትን ሰዎች በሚወጉ የሕዝቦች ሠራዊት ላይ ይህ ይሆናል' (ምትክ ስም ተመልከት)