1.3 KiB
1.3 KiB
የወራሪዎችሽ ብዛት እንደ ደቀቀ ትቢያ፣ የጨካኞችም ብዛት እንደሚያልፍ ገለባ ይሆናል
ወራሪው ሠራዊት በእግዚአብሔር ምን ያህል ደካማና እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር የወራሪዎችሽን ብዛትና የጨካኞቹን ብዛት በቀላሉ ያስወግዳል፡፡' (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)
የወራሪዎችሽ ብዛት
ጥቃት የሚያደርሱብህ ብዙ ወታደሮች
ጨካኞቹ … እንደ ገለባ
ተርጓሚው "ይሆናሉ' የሚለውን ማሰሪያ አንቀጽ መጠቀም ይችላል፡፡ አት፡- "ምሕረት የማያሳዩሽ ወታደሮች እንደ ገለባ ይሆናሉ' (መቅረታቸው አሳቡን ከመረዳት ስለማያጓድሉ የተዘለሉ ተመልከት)
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ አንቺ ይመጣል
አንቺ የሚለው ቃል የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ያመልክታል፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሊረዳሽ ይመጣል' ወይም 2) "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሊቀጣሽ ይመጣል' (የ "አንተ' ልዩ ልዩ አጠቃቀሞች)