am_tn/isa/29/03.md

1.9 KiB

በዙሪያሽም እሰፍራለሁ

በዚህ ውስጥ "እኔ' የሚለው እግዚአብሔርን ያመለክታል፡ ይህ እግዚአብሔር የጠላትን ሠራዊት ኢየሩሳሌምን እንዲከቡ ማድረጉን ይወክላል፡፡ አት፡- "የጠላቶችሽን ሠራዊት እንዲከቡሽ አዝዛለሁ' (ምትክ ቃል ተመልከት)

ቅጥር … የከበባ ሥራ

"ቅጥር' ከረጃጅም ግንቦች ከተሞችን ለማጥቃት ሠራዊቶች የሚገነቡት ማማ ነው፡፡ "የከበባ ሥራዎች' ከተሞችን ለማጥቃት ሠራዊቶች የሚገነቧቸውን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ያመለክታል፡፡ (የማይታወቁትን ስለመተርጎም ተመልከት)

ትዋረጂማለሽ

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ጠላትሽ ወደ ታች ያወርድሻል ወይም ጠላትሽ ዝቅ ያደርግሻል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

በመሬትም ላይ ሆነሽ ትናገሪያለሽ፣ ቃልሽም ዝቅ ብሎ ከአፈር ይወጣል፣ ድምጽሽም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መናፍስት ጠሪ ድምጽ ይሆናል፣ ቃልሽም ከአፈር ወጥቶ ይጮኻል

በመሠረቱ እነዚህ ሁሉ ዐረፍት ነገሮች የሚናገሩት ስለ አንድ ነገር ነው፡፡ አንድ ወቅት በትዕቢት ቃላት ይናገሩ የነበሩ ሰዎች ጠላታቸው ካሸነፋቸው በኋላ ደካሞችና ሐዘንተኞች እንደሚሆኑ አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አት፡- "ሙታን ከሚያድሩበት ስፍራ መንፈስ እንደሚናገረ እንዲሁ በደካማና የሽክሹክታ ድምፅ ብቻ ትናገራላችሁ' (ዘይቤአዊ ንግግርና አጓዳኝነት ተመልከት)