am_tn/isa/28/25.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ለኢየሩሳሌም ሕዝብ ምሳሌውን መንገሩን ይቀጥላል፡፡ (ምሳሌዎች ተመልከት)

እርሻውን ባስተካከለ ጊዜ

ገበሬው መሬቱን ባረሰ ጊዜ

ጥቁሩን አዝሙድ፣ ከሙኑንም፣ ስንዴውንም በተርታ፣ ገብሱንም በስፍራው፣ አጃንም በዳርቻው የሚዘራ አይደለምን

ኢሳይያስ የኢየሩሳሌም ሰዎች በጥልቀት እንዲያስቡ ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ ቋንቋህ ለእያንዳንዱ የዘር ዓይነት ቃል ከሌለው ጠቅለል ተደርገው ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ አት፡- "በእርግጥ እያንዳንዱን የዘር ዓይነት በትክክለኛው መንገድና በተገቢው ቦታ ይተክላል፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)

አዝሙድ … ከሙን

እነዚህ የቅመማ ቅመም ተክሎች ስሞች ናቸው፡፡ (የማይታወቁትን ስለመተርጎም ተመልከት)

ስንዴ … ገብስ … አጃ

እነዚህ የእህል ተክሎች ስሞች ናቸው፡፡ ተርጓሚዎች በአጠቃለይ የእህል የዘር ዓይነቶች በሚል ሊወክሏቸው ይችላሉ፡፡ (የማይታወቁትን ስለመተርጎም ተመልከት)

ይህንም ብልሃት አምላኩ ያስታውቀዋል ያስተምረዋልም

በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች አንድ ነገር ይናገራሉ፡፡ አት፡- "ገበሬው እያንዳንዱን የተክል ዓይነት እንዴት መንከባከብ እንዳለበት እንዲያውቅ እግዚአብሔር ይረዳዋል' (አጓዳኝነት ተመልከት)