am_tn/isa/28/23.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህ በ28፡29 የሚያልቀውን ምሳሌ ይጀምራል፡፡ (ምሳሌዎች ተመልከት)

አድምጡ ድምፄንም ስሙ፣ልብ አድርጉ ንግግሬንም ስሙ

በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚናገሩት አንድ ነገር ነው፡፡ ሁለተኛው ሐረግ የመጀመሪያውን ለማጠናከር ጥቅም ላይ የዋለ ነው፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)

ድምፄንም

በዚህ ስፍራ ድምፅ የሚለው ኢሳይያስ የተናገረውን ይወክላል፡፡ አት፡- "ለተናገርኩት' (ምትክ ቃል ተመልከት)

ንግግሬንም

መልእክቴንም

ለመዝራት ቀኑን ሙሉ የሚያርስ ገበሬ ሁልጊዜ ያርሳልን? ወይስ ሁልጊዜ እርሻውን ይገለግላልን? ጓሉንስ ይከሰክሳልን?

ሕዝቡ በጥልቀት እንዲያስብ ኢሳይያስ አሳብ ገላጭ ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ አት፡- "ገበሬ ዘርን ሳይዘራ መሬትን ደግሞ ደጋግሞ አያርስም ያለማቋረጥም አፈሩ ላይ አይሰራም' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)