am_tn/isa/28/20.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ መናገሩን ይቀጥላል፡፡

ሰው በእርሱ ላይ ተዘርግቶ ቢተኛ አልጋው አጭር ነው፤ ሰውም ሰውነቱን መሸፈን ቢወድድ መጎናጸፊያ ጠባብ ነው

ይህ ምናልባት ሕዝቡ በዚያ ዘመን የሚያውቀው ምሳሌ ነው፡፡ በጣም አጭር እንደሆነ አልጋ ወይም በጣም ጠባብ እንደሆነ መጎናጸፊያ ከእግዚአብሔር ቅጣት በሳለም ይጠብቀናል ብለው የተማመኑበት ያሳዝናቸዋል፡፡ (ምሳሌዎች ተመልከት)

እግዚአብሔር ይነሣል

እግዚአብሔር ለሥራ መዘጋጀቱ ተቀምጦ እንደነበረና እንደሚነሣ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡

በፐራሲም ተራራ … በገባዖንም ሸለቆ

እነዚህ እግዚአብሔር የጠላትን ሠራዊት በተዓምራት ያሸነፈባቸውን ቦታዎች ያመለክታሉ፡፡ (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ እና የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)

ራሱን ይቀሰቅሳል

"ይቆጣል

እንግዳ ሥራውን … ያልታወቀ አድራጎቱን

እነዚህ ሁለት ሐረጎች አንድ ነገር ይናገራሉ፡፡ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ጠላቶቻቸውን እንዲያሸንፉ ከመርዳት ይልቅ የኢየሩሳለምን ሕዝብ ለማሸነፍ እግዚአብሔር የጠላትን ሠራዊት መጠቀሙ እንግዳ ሥራ ነው፡፡