am_tn/isa/28/18.md

2.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ መናገሩን ይቀጥላል፡፡

ከሞትም ጋር ያደረጋችሁት ቃል ኪዳን ይፈርሳል፣ ከሲኦልም ጋር የተማማላችሁት መሐላ አይቆምም

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ከሞት ጋር ያላችሁን ቃል ኪዳን ከሲኦልም ጋር ያላችሁን ስምምነት እሰርዘዋለሁ፡፡' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ከሞት ጋር … ቃልኪዳን … ከሲኦልም ጋር ስምምነት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) የኢየሩሳሌም መሪዎች የሙታን መኖሪያ አማልክት ከመሞት እንዲጠብቋቸው ከእነርሱ ጋር ስምምነት ለማድረግ በመጣር አስማትና ጥንቆላ ተጠቅመዋል ወይም 2) ይህ መሪዎቹ ከግብጽ መሪዎች ጋር ስምምነት ማድረጋቸውን የሚገልጽ ስዕላዊ ንግግር ነው፡፡ የኢየሩሳሌም መሪዎች ከሙታን መኖሪያ አማልክት ጋር ስምምነት እንዳደረጉ ሁሉ ግብጻውያንም ጥበቃ ማድረግ እንደሚችሉ ተማምነዋል፡፡ ይህንን በኢሳይያስ 28፡15 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት (አጓዳኝነትና ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

አይቆምም

"አይጸናም'

የሚጠራርግ ጎርፍ ባለፈ ጊዜ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ጎርፍ ጥፋት ሊያደርስ የሚችል የትኛውንም ነገር በአጠቃለይ የሚወክል ተለዋጭ ስም ነው ወይም 2) ጎርፍ የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ለማጥፋት እግዚአብሔር የሚልከውን የጠላት ሠራዊት የሚያመለክት ስዕላዊ ንግግር ነው (ተለዋጭ ስምና ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

በእርሱ ትጥለቀለቃላችሁ

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ያጥለቀልቃችኋል' ወይም "ያጠፋችኋል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ማለዳ ማለዳ

ይህ ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "በየቀኑ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

ቀንና ሌሊት

"ሙሉ ቀኑን' ማለት ነው፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)