am_tn/isa/28/17.md

2.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እግዚአብሔር ለሕዝቡ በኢየሩሳሌም የሚያደርገውን ሕንፃን ከሚመሠርት ገንቢ ጋር ማነጻጸሩን ይቀጥላል፡፡ (ኢሳይያስ 28፡16)

ለመለኪያ ገመድ ፍትህን ለቱምቢም ጽድቅን አደርጋለሁ

ሕዝቡ ፍትሐዊና ጻድቅ መሆኑን ለመወሰን እግዚአብሔር በፍርዱና በጽድቁ መሠረት መፈተኑ አንድ ነገር ተገቢ ቁመት ያለውና ፍጽም የተስተካከለ መሆኑን ለመወሰን መለኪያ መሣሪያዎች እንደሚጠቀም ግንበኛ ተደርጎ ተገልጾአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

መለኪያ ገመድ

ግንበኛ የአንድ ነገር ቁመት ትክክል እንደሆነ ለመወሰን መለኪያ ገመድ ይጠቀማል፡፡

ቱምቢ

ግንበኛ አንድ ነገር ቀጥ ያለና የተስተካከለ መሆኑን ለመወሰን ቱምቢ ይጠቀማል፡፡

በረዶ ጠርጎ ይወስደዋል

እግዚአብሔር ከፍተኛ መጠን ያለው በረዶ እንዲወርድ ማድረጉ የሚያጠለቀልቅ ጎርፍ እንደሚሆን ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "የበረዶ ዶፍ ያጠፋል' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

በረዶ … የውኃ ሙላት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ጥፋትን የሚያስከትል የትኛውንም ነገር በአጠቃለይ የሚወክሉ ተለዋጭ ስሞች ናቸው ወይም 2) የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ለማጥፋት እግዚአብሔር የሚልከውን የጠላት ሠራዊት የሚያመለክት ስዕላዊ ንግግር ነው (ተለዋጭ ስምና ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

የውሸቶች መሸሸጊያ … መሰወሪያ

ይህ ውሸቶች ሰው ሄዶ እንደሚሸሸግባቸው ቦታ አድርጎ ይናገራል፡፡ የኢየሩሳሌም መሪዎች ከእግዚአብሔር ቁጣ ይጠብቀናል ብለው የታመኑበትን ይወክላሉ፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) መሪዎቹ ራሳቸውን ለመጠበቅ በተናገሩት በገዛ ራሳቸው ውሸቶች ይታመናሉ ወይም 2) መሪዎቹ በሰላም እንዲጠብቃቸው ከሙታን መኖሪያ የሐሰት አማልክት ጋር ባደረጉት ቃል ኪዳን ይታመናሉ ወይም 3) መሪዎቹ በሰላም እንዲጠብቃቸው ከግብፃውያን ጋር ባደረጉት ስምምነት የታመናሉ፡፡ ተመሳሳይ ሐረግ በኢሳይያስ 28፡15 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ (ስዕላዊ ንግግር እና እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)