am_tn/isa/28/14.md

2.9 KiB

ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ

"ስለዚህ የእግዚአብሔርን መልእክት ስሙ'

ከሞት ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፣ ከሲኦልም ጋር ተስማምተናል

በመሠረቱ ሁለቱም አረፍተ ነገሮች የሚናሩት አንድ ነገር ነው፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) የኢየሩሳሌም መሪዎች የሙታን መኖሪያ አማልክት ከመሞት እንዲጠብቋቸው ከእነርሱ ጋር ስምምነት ለማድረግ በመጣር አስማትና ጥንቆላ ተጠቅመዋል ወይም 2) ይህ መሪዎቹ ከግብጽ መሪዎች ጋር ስምምነት ማድረጋቸውን የሚገልጽ ስዕላዊ ንግግር ነው፡፡ የኢየሩሳሌም መሪዎች ከሙታን መኖሪያ አማልክት ጋር ስምምነት እንዳደረጉ ሁሉ ግብጻውያንም ጥበቃ ማድረግ እንደሚችሉ ተማምነዋል፡፡ (አጓዳኝነትና ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

የሚያጥለቀልቅ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም

ይህ የእግዚአብሔር ፍርድና ቅጣት ሕዝቡን እንደሚመታ ጅራፍ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ ጅራፉም በኢየሩሳሌም እንደሚያልፍ ጎርፍ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "ስለዚህም ሰው ሁሉ ሲሰቃይና ሲሞት፣ የሚጎዳን ምንም ነገር የለም፡፡' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ውሸትን መሸሸጊያችን አድርገናልና፣ በሐሰትም ተሰውረናልና

በመሠረቱ ሁለቱም ሐረጎች የሚናገሩት አንድ ነገር ነው፡፡ ወሸት እና ሐሰት ሰው ሄዶ እንደሚሸሸግባቸው ቦታ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ በኢየሩሳሌም የሚገኙ መሪዎች በውሸት እንደሚታመኑ አልተናገሩም፡፡ በእርግጥ ደኅንነታቸው አስተማማኝ አንደሆነ አምነዋል፡፡ ነገር ግን በውሸት ስለታመኑ ደኅንነታቸው አስተማማኝ እንዳልሆነ ኢሳይያስ ያውቃል፡፡ አት፡- "ውሸትና ሐሰት ከአደጋ ልንሸሸግባቸው እንደምንችልባቸው ቦታ ሆነዋልና' (አጓዳኝነትና ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ውሸትን መሸሸጊያችን … በሐሰትም ተሰውረናልና

ሊሆኑየሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) መሪዎቹ ራሳቸውን ለመጠበቅ በዋሹአቸው በገዛ ራሳቸው ውሸቶች ይታመናሉ ወይም 2) መሪዎቹ ከሙታን መኖሪያ ሐሰተኛ አማልከት ጋር ያደረጉት ኪዳን በሰላም እንደሚጠብቃቸው ይታመናሉ ወይም 3) መሪዎቹ ከግባጻውያን ጋር ያደረጉት ስምምነት በሰላም እንደሚጠብቃቸው ይታመናሉ