am_tn/isa/28/13.md

1.5 KiB

ስለዚህ … የእግዚአብሔር ቃል

ስለዚህ … የእግዚአብሔር መልእክት

ትእዛዝ በትእዛዝ፣ ትእዛዝ በትእዛዝ፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ

አነዚህ ኢሳይያስ እንዴት እያስተማራቸው እንዳለ ለመተቸት ሰካራሞቹ ነቢያትና ካህናት የሚጠቀሙባቸው ቃላት ናቸው፡፡ ይህንነ በኢሳይያስ 28፡10 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፣ እንዲሰበሩም፣ እንዲጠመዱ፣ እንዲማረኩም

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "የአሦር ሠራዊት ይመጣና ያሽንፋቸው፣ ምርኮኞችም አድርጎ ይወስዳቸው ዘንድ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፣ እንዲሰበሩም

ሕዝቡ በጦርነት በጠላት ሠራዊት መሸነፉ ሕዝቡ እንደሚወደቅና እንደሚሰበር ተደርጎ ተነገሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

እንዲጠመዱ

የእስራኤልን ሕዝብ የሚማርኩ የጠላት ወታደሮች እንሰሳን በወጥመድ እንደሚያጠምዱ አዳኞች ተደርገው ተገልጸዋል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)