am_tn/isa/28/11.md

1.5 KiB

ለዚህ ሕዝብ በሚያላግጡ ከንፈሮችና በባዕድ ልሳን ይናገራል

በዚህ ስፍራ "ከንፈሮች' እና "ልሳን' የሚለው እስራኤላውያን ከሚናገሩት የተለየ ቋንቋ የሚናገሩትን ባዕዳን ይወክላል፡፡ ይህ እስራኤላውያንን የሚወጋውን የአሦራውያንን ሠራዊት እንደሚያመልክት ይጦቅማል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ለዚህ ሕዝብ የባዕድ ቋንቋ በሚናገሩ የጠላት ወታደሮች አማካይነት ይናገራል፡፡' (ተለዋጭ ስም እና አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

የሚያላግጡ ከንፈሮች

"የሚንተባተቡ ከንፈሮች'

ዕረፍት ይህች ናት

"ዕረፍት' የሚለው የነገር ስም በማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ይህ ማረፊያ ቦታ ነው፡፡' (የነገር ስም ተመልከት)

ለደከመው ዕረፍት ስጡ

"ዕረፍት' የሚለው የነገር ስም በማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "የደከመው ማንም ይምጣና ይረፍ' (የነገር ስም ተመልከት)

ይህችም ማረፊያ ናት

ማረፊያ የሚለው የነገር ስም በማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ይህ ልትታደስ የምትችልበት ቦታ ነው' (የነገር ስም ተመልከት)