am_tn/isa/28/09.md

1.3 KiB
Raw Permalink Blame History

እውቀትን ለማን ያስተምራል ወይስ መልእክቱን ለማን ያብራራል

ሰካራሞቹ ነቢያትና ካህናት ሊያርማቸው የሚፈልገውን ኢሳይያስን ለመተችት ጥያቄ ይጠቀማሉ፡፡ አት፡- "ሰካራሞቹ ነቢያትና ካህናት፣ ‘ኢሳይያስ ስለ እግዚአብሔር መልእክት ሊያስተምረን እየሞከረ አይደለምን! ይላሉ' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)

ወተትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን

እንደ ሕፃናት እንደተመለከታቸው ስለተሰማቸው ሰካራሞቹ ነቢያትና ካህናት ኢሳይያስን ለመተቸት ጥያቄ ይጠቀማሉ፡፡ አት፡- "እንደ ሕፃናት ሊመለከተን አይገባም' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ እና አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ትእዛዝ በትእዛዝ፣ ትእዛዝ በትእዛዝ፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ

ለሕፃን እንደሚናገር ኢሳይያስ ቀላል ትእዛዛትን እንደሚደጋግም ስለተሰማቸው ሰካራሞቹ ነቢያትና ካህናት ኢሳይያስን ይተቻሉ፡፡