am_tn/isa/28/07.md

1.7 KiB

ነገር ግን እነዚህም እንኳን

"ነገር ግን መሪዎቹ እንኳን'

ካህኑና ነቢዩ

ይህ አንድ የተወሰነ ካህን ወይም ነቢይ ማለት አይደለም፡፡ ካህናትንና ነቢያትን በአጠቃላይ ያመለክታል፡፡ አት፡- "ካህናትና ነቢያት' (አጠቃላይ ስማዊ ሐረጎች ተመልከት)

ከወይን ጠጅ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፣ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንደፋደፋሉ

እነዚህ ሁለት ሃረጎች በመሠረቱ የሚናገሩት ስለ አንድ ነገር ሲሆን ሰካራሞች ከመሆናቸው የተነሣ ካህናቱና ነቢያቱ ሥራቸውን መሥራት እንዳልቻሉ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አት፡- "ሰካራሞች ስለሆኑ በየአካባቢው ይንገዳገዳሉ' (አጓዳኝነት ተመልከት)

በወይን ጠጅም ይዋጣሉ

በተገቢው ሁኔታ ማሰብ እስከማይችሉ ድረስ ይጠጡ ስለነበር የወይን ጠጅ እንደዋጣቸው ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "የወይን ጠጅ እንዲደነጋገርባቸው አደርጓል' (ሰስዕላዊ ንግግርና አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

በራእይ ይንገዳገዳሉ በፍርድም ይደነቃቀፋሉ

በትክክል ለመራመድ አብዝተው እንደሚጠጡ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ራእይ ለመረዳት ወይም መልካም ፍርድ ለማድረግ አብዝተው ይጠጣሉ፡፡