am_tn/isa/28/05.md

1.9 KiB

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር

ይህንን በኢሳይያስ 1፡9 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

ውብ ዘውድና የውበት አክሊል ይሆናል

እንደ እውነተኛ ንጉሣቸው ለብሰውት ለሚያከብሩት ሕዝብ እግዚአብሔር ውብ ዘውድ እንደሚሆን ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ውብ ዘውድና የውበት አክሊል

የሁለቱም ትርጉም አንድ ነው፡፡ አት፡- "ውብ ዘውድ' (የሁለት ነገሮች ተመሳሳይነት ተመልከት)

ሕዝብ፣ በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጥም የፍትህ መንፈስ፣ … ብርታትም

እንደ "ፍትህ' እና "ብርታት' ያሉ የነገር ስሞች በቅጽልነት እንዲገለጹ ይህ እንደገና ሊጻፍ ይችላል፡፡ አት፡- "ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ዳኞችን ጻድቃን እንዲሆኑ ያደርጋል እንዲሁም ብርቱዎች ያደርጋቸዋል' (የነገር ስም ተመልከት)

የፍትህ መንፈስ

የፍትህ መንፈስ ያለው ሰው የፍትሃዊነት ባሕርይ ያለውና ጻድቅ ሰው ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጥ

ይህ ፈሊጣዊ ንግግር የዳኝነት ሥልጣን ያለው ሰው ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

በበራቸው ጠላቶቻቸውን ወደ ኋላ ለሚመልሱ ብርታትን

በዚህ ስፍራ "ወደ ኋላ ለሚመልሱ' የሚለው በጦርነት ለሚያሸነፉ የሚል ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "ጠላቶች ከተማቸውን ሲያጠቁ ጠላቶቻቸውን ያሸንፉ ዘንድ እግዚአብሔር ወታደሮቹን ብርቱዎች ያደርጋቸዋል' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)