am_tn/isa/28/03.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ኢሳይያስ የሰማሪያ ሕዝበና ከተማ አክሊል እንደሆኑ አድርጎ መናገሩን ይቀጥላል፡፡ (ኢሳይያስ 28፡1-2 ተመልከት)

የኤፍሬም ሰካራሞች ትዕቢት አክሊል በእግር ይረገጣል

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "የጠላት ሠራዊት አበባን በእግራቸው እንደሚያደቅቁ የሰማሪያን ትዕቢተኛ ሰካራሞች ያደቅቋቸዋል፡፡' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

የኤፍሬም … ትዕቢት አክሊል … በወፍራሙ ሸለቆ ራስ ላይ ያለች

"አክሊል' ከአበባ የተሠራ ዘውድ ነው፡፡ በዚህ ስፍራ ከለምለሙ ሸለቆ በላይ የተቀመጠችውን፣ የእስራኤልን ዋና ከተማ፣ የሰማሪያ ከተማን ይወክላል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

የረገፈች … ከመከር በፊት አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች

ይህ ከመከር በፊት የበሰለች በለስን እንዳየና ፈጥኖ እንደሚበላ ሰው የጠላት ወታደሮች የሰማሪያን ውበት እንደሚያዩና ፈጥነው እንደሚበዘብዟት ይናገራል፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)