am_tn/isa/24/21.md

1.7 KiB

በዚያም ቀን

"በዚያን ጊዜ'

የሰማይ ሠራዊት

ሠራዊት ሲል የጦር ሠራዊት ነው፡፡ በዚህ ስፍራ "የሰማይ ሠራዊት' የሚለው በሰማይ የሚገኙትን ብዙዎች ኃያላን መናፍስት ያመለክታል፡፡ ክፉዎች እንደሆኑ በግልጽ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ አት፡- "ኃያላን አካላት' ወይም "ክፉ መንፈሳዊያን አካላት' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

በሰማያት

"በሰማይ

ግዞተኞች በጉድጓድ እንደሚከማቹ በአንድነት ይከማቻሉ

በዚህ ስፍራ "ጉድጓድ' የሚለው በወህኒ ቤት የሚገኝን ጨለማ ክፍል ወይም ጉድጓድ ያሳያል፡፡ አት፡- እግዚአብሔር እንደ እስረኞቹ በአንድ ላይ ይሰበስባቸዋል በወህኒውም አንደኛው ክፍል ይቆልፍባቸዋል፡፡ (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ይቀጣሉ

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ይቀጣቸዋል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ጨረቃ ያፍራል፣ ፀሐይም ይዋረዳል

ጨረቃና ፀሐይ ታላቅ ኃይል ካለው ሰው ፊት ከመሆኑ የተነሳ እንዳፈረ ሰው ተደርገው ተገልጸዋል፡፡ እግዚአብሔር ባለበት የጨረቃና የፀሐይ ብርሃን ይደበዝዛል፡፡ (ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየት ተመልከት)