am_tn/isa/24/17.md

2.0 KiB

በምድር ላይ የምትኖሩ ሆይ፣ ፍርሃት፣ ገደልና ወጥመድም በእናንተ ላይ ነው

"በምድር ላይ የምትኖሩ ሰዎች ፍርሃት፣ ገደልና ወጥመድ ይገጥማችኋል'

ከገደል .. በወጥመድ ይያዛል

በዚህ ስፍራ ገደልና ወጥመድ የሚሉት ሕዝቡ ላይ ሊሆኑ ያሉትን የተለያዩ ክፉ ነገሮች ይወክላሉ፡፡ ሰዎች አንድን ክፉ ነገር ለማምለጥ ይሸሻሉ ነገር ግን ሌላ ክፉ ነገር ይገጥማቸዋል፡፡ (ተለዋጭ ስም ተመልከት)

የሽብር ድምጽ

"አስፈሪ ድምጽ'

በወጥመድ ይያዛል

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ወጥመዱ ይይዘዋል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

የሰማይ መስኮቶች ይከፈታሉ

ይህ እግዚአብሔር የሰማይ መስኮትን እንደሚከፍትና በእርሱ አማካይነት ውኃ እንዲፈስስ እንደሚያደርግ ዓይነት ብዙ መጠን ያለው ዝንብ ከሰማይ እንደሚወርድ ይናገራል፡፡ አት፡- "ሰማይ ይከፈታል የዝናብም ዶፍ ይወርዳል' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

የምድር መሠረቶችም ይናወጣሉ

በተለምዶ "መሠረት' የሚለው ቃል ከሥር ሆኖ ለአንድ ሕንፃ ድጋፍ የሚሰጥን የድንጋይ ክፍል (መዋቅር) ያመለክታል፡፡ በዚህም ስፍራ ምድርን በቦታዋ ደግፎ ወይም ይዞ እንዳቆመ ይታሰብ የነበረን ተመሣሣይ መዋቅር ይገልፃል፡፡ ኢሳይያስ ምድርን ደግፎ የያዛት መዋቅር እንኳን ይናወጣል ይላል፡፡ አት፡- "በጣም በሚያስፈራ ሁኔታ ምድር ትናወጣለች' ወይም "በጣም የሚያስፈራ የምድር መንቀጥቀጥ ይሆናል'