am_tn/isa/24/14.md

2.5 KiB

ድምፃቸውን ያነሣሉ፣ ስለ እግዚአብሔርም ክብር ይጮኻሉ

ድምፃቸውን ያነሣሉ የሚለው ሃረግ ድምፅን ከፍ አድርጎ መናገር የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "ለእግዚአብሔር ክብር ይዘምራሉ ይጮኻሉም' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

… ያነሣሉ … ይጮኻሉ

በዚህ ስፍራ … ያነሣሉ … ይጮኻሉ የሚለው እግዚአብሔር ምድርን ካጠፋት በኋላ ገና በሕይወት ያሉትን ያመለክታል፡፡

በደስታ ከባሕር ይጮኻሉ

በዚህ ስፍራ "ባሕር' የሚለው ከእስራኤል በምዕራብ የሚገኘውን የሜዲትራንየንን ባሕር ያመለክታል፡፡ አት፡- "በምዕራብም ወደ ባሕሩ ሲል የሚኖሩ በደስታ ይጮኻሉ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

ስለዚህ በምሥራቅ እግዚአብሔርን አክብሩ

በምሥራቅ የሚለው ሃረግ ከእስራኤል በስተ—ምሥራቅ የሚኖሩትን ሰዎች ይወክላል፡፡ ኢሳይያስ እነዚህ ሕዝቦች ከእርሱ ጋር እንዳሉ አድርጎ ያዝዛቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚናገረው እግዚአብሔር ምድሪቱን ካጠፋ በኋላ ወደፊት ለሚኖሩት ሰዎች ነው፡፡ አት፡- "ስለዚህ በስተ ምሥራቅ በሩቅ ምድር የሚኖሩ ሁሉ እግዚአብሔርን ያከብራሉ' (ምትክ ቃል፣በስፍራው ለሌለ ወይም እንደ ሰው ለተወሰደ ግዑዝ ነገር መናገርና ትንቢታዊ አላፊ ጊዜ ተመልከት)

በባሕር ደሴቶች ክብር ስጡ

ኢሳይያስ በሜዲትራንየን ደሴቶች ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ከእርሱ ጋር እንዳሉ አድርጎ ያዝዛቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚናገረው እግዚአብሔር ምድሪቱን ካጠፋ በኋላ ለሚኖሩት ሰዎች ነው፡፡ አት፡- "በደሴቶች የምትኖሩ ሁሉ ክብር ስጡ' (ምትክ ቃል፣በስፍራው ለሌለ ወይም እንደ ሰው ለተወሰደ ግዑዝ ነገር መናገርና ትንቢታዊ አላፊ ጊዜ ተመልከት)

ለእግዚአብሔር ስም

በዚህ ስፍራ ስም እግዚአብሔርን ይወክላል፡፡ አት፡- "ለእግዚአብሔር' (ምትክ ቃል ተመልከት)