am_tn/isa/24/12.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃዎች፡-

ኢሳይያስ እግዚአብሔር በምድር ላይ በሚፈርደበት ጊዜ የሚሆነውን የወደፊቱን ጊዜ መግለጹን ቀጠለ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ነቢያት የወደፊቱን ጊዜ ሁኔታ ባላፊ ወይም በአሁን ጊዜ እንደሆነ ነገር አድርገው ይገልጻሉ፡፡ ይህ ሁኔታው በእርግጥ እንደሚፈጸም አጽንዖት ይሰጣል፡፡ (ትንቢታዊ አላፊ ጊዜ ተመልከት)

ከተማይቱም ባድማ ሆናለች

ባድማ የሚለው የነገር ስም ሰው የማይኖርበት ወይም ባዶ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ከተማይቱ ሰው የማይኖርባት ሆነች' ወይም "ከተማይቱ ባዶዋን ቀረች' (የነገር ስም ተመልከት)

ከተማይቱ

ይህ የተወሰነ አንድ ከተማን ሳይሆን ከተሞችን በአጠቃላይ ነው፡፡ (አጠቃላይ ስማዊ ሐረጎች ተመልከት)

የወይራን ዛፍ እንደ መምታት፣ ከወይንም መከር በኋላ ቃርሚያውን እንደ መልቀም

ይህ እግዚአብሔር ምድሪቱን ካጠፋት በኋላ፣ ሕዝቡን ፍሬያቸው ከተለቀመ ዛፎችና የወይን ተክሎች ጋር ያስተያያል፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)