am_tn/isa/24/06.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃዎች

ኢሳይያስ እግዚአብሔር በምድር ላይ በሚፈርደበት ጊዜ የሚሆነውን የወደፊቱን ጊዜ መግለጹን ቀጠለ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ነቢያት የወደፊቱን ጊዜ ሁኔታ ባላፊ ወይም በአሁን ጊዜ እንደሆነ ነገር አድርገው ይገልጻሉ፡፡ ይህ ሁኔታው በእርግጥ እንደሚፈጸም አጽንዖት ይሰጣል፡፡ (ትንቢታዊ አላፊ ጊዜ ተመልከት)

እርግማን ምድርን ትበላለች

የእግዚአብሔር ምድርን መርገምና ማጥፋት ምድርን ፈጽሞ እንደሚበላ የዱር አውሬ ወይም ምድርን ፈጽሞ እንደሚያቃጥል እሳት ዓይነት እንደሆነ እንደ መርገም ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (ሥዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ነዋሪዎቿ በደለኞች ሆነው ተገኝተዋል

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዘአብሔር ሕዘቡ በደለኛ መሆኑን ያስታውቃል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)