am_tn/isa/24/03.md

1.7 KiB

ምድር ፈጽማ ትጠፋለች፣ ትገፈፋለችም

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ምድርን ፈጽሞ ያጠፋታል፣ የከበረውንም ነገር ሁሉ ያስወግዳል፡፡' (አጓዳኝነት ተመልከት)

እግዚአብሔር ይህን ቃል ተናግሮአል

"እግዚአብሔር ይህን አደርጋለሁ አለ'

ምድር ደረቀች ጠወለገችም፣ ዓለም ደረቀች ከሰመችም

በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሃረጎች ተመሣሣይ ነገር ይናገራሉ፡፡ አት፡- በምድር ያለ ነገር ሁሉ ይደርቃል ይሞታልም (አጓዳኝነት ተመልከት)

ምድር … ዓለም

ሁለቱም በምድር ላይ ያለውን ነገር ሁሉ ይወክላሉ፡፡ (ምትክ ስም ተመልከት)

ምድር በነዋሪዎቿ ረክሳለች

ሕዝቡ ኃጢአት መሥራታቸውና ምድር በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖራት ማድረጋቸው ሕዝቡ ምድርን በተጨባጭ እንድትቆሽሽ እንዳደረጓት ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ሕዝቡ ምድርን አረከሷት' (ስዕላዊ ንግግር፣ አደራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ሕግጋቱን ጥሰዋል፣ ሥርዓቱን ተላልፈዋል፣ የዘላለሙንም ኪዳን አፍርሰዋል

የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ሥርዓት አልታዘዙም፣ የእግዚአብሔርንም ዘላለማዊ ኪዳን አፍርሰዋል