1.4 KiB
1.4 KiB
ምድርን ባዶ ለማድረግ
"ምድርን ባድማ ለማድረግ' ወይም "በምድር ያለውን ነገር ሁሉ ለማጥፋት'
እነሆ
ይህ ቃል አስፈላጊ ሁናቴን ያመላክታል፡፡ ቋንቋህ ይህን የሚያደርግበት መንገድ ካለው፣ በዚህ ስፍራ ለመጠቀም ልታጤነው ትችላለህ፡፡
እንደ … እንዲሁ
እግዚአብሔር ሊያደርገው ያለው ነገር አልተገለጸም፣ ነገር ግን ይታወቃል፡፡ ይህ እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ በተመሳሳይ መንገድ እንደሚመለከት ያሳያል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር እንደሚበትን … እንዲሁ ይበትናል' (መቅረታቸው አሳቡን ከመረዳት ስለማያጓድሉ የተዘለሉ)
ካህኑ … አራጣ ተቀባዩ
ኢሳይያስ በ24፡2 የተወሰኑ የሕዝቡን የመደብ ክፍሎች ይዘረዝራል፡፡ በዩዲቢ እንደሚገኘው በብዙ ቁጥር ስሞች ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ካህናቱ … አራጣ ተቀባዮቹ' (አጠቃላይ ስማዊ ሐረጎች)
አራጣ ተቀባዩ
"ገንዘብ ያበድረው፡፡' አራጣ ማለት አንድ ሰው ገንዘብ ስለተበደረ ሊከፍለው የሚገባ ተጨማሪ ገንዘብ ማለት ነው፡፡
አራጣ ከፋዩ
"ገንዘብ የተበደረው'