am_tn/isa/23/17.md

1.8 KiB

በኋላም እንዲህ ይሆናል

አንድ አስፈላጊ ሁኔታ ሊሆን እንዳለ ለማመልከት ይህ ሐረግ በዚህ ስፍራ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ቋንቋህ ይህን የሚያደርገበት መንገድ ካለው በዚህ ስፍራ ልትጠቀምበት ትችላለህ፡፡

ሰባ ዓመታት

"70 ዓመታት' (ቁጥሮች ተመልከት)

እግዚአብሔር ጢሮስን ይጎበኛታል

በዚህ ስፍራ ጢሮስ የሚለው በጢሮስ የሚኖረውን ሕዝብ ይወክላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር በጢሮስ የሚኖረውን ሕዝብ ይጎበኛል' (ምትክ ቃል ተመልከት)

ከምድር … የግልሙትናን ሥራ በመሥራት እንደገና ገንዘብ ማትረፍ ትጀምራለች

ኢሳይያስ የጢሮስን ሕዝብ ከጋለሞታ ጋር ያመሳስላል፡፡ ጋለሞታ ለገንዘብ ስትል ለማንኛውም ወንድ ራሷን እንደምትሸጥ እንደዚያው የጢሮስም ሕዝብ ከ(ለ)ሁሉም መንግሥታት ይገዛሉ ይሸጣሉ፡፡ አት፡- እንደጋለሞታም ከምድር መንግሥታት ሁሉ ጋር ይገዛሉ ይሸጣሉም፡፡ (ምትክ ቃል ተመልከት)

በግምጃ ቤት አይከማችም ወይም አይጠበቅም

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ነጋዴዎቹ ገንዘባቸውን ሰውረው አያከማቹም' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

በእግዚአብሔር ፊት ለሚኖሩ

"እግዚአብሔርን ለሚታዘዙና ለሚያገለግሉ'

የተትረፈረፈ ምግብ ለእነርሱ ለማቅረብ

"የሚመገቡት በቂ ምግብ ይኖራቸው ዘንድ'