am_tn/isa/23/15.md

1.7 KiB

በዚያ ቀን

"በዚያ ጊዜ' ወይም "በመቀጠል'

ጢሮስ ለሰባ ዓመት የተረሳች ትሆናለች

ከእንግዲህ ወዲያ ለመግዛትና ለመሸጥ ሕዝቡ ወደ ጢሮስ የማይሄድ እስከሆነ ድረስ፣ ከተማይቱን የመርሳት ያህል ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ለሰባ ዓመታት ሕዝቡ ጢሮስን የመርሳት ያህል ይዘነጋታል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልክት)

ለሰባ ዓመታት

"ለ70 ዓመታት' (ቁጥሮች ተመልከት)

እንደ አንድ ንጉሥ ዘመን

"እንደ አንድ ንጉሥ ዓመታት' ወይም "አንድ ንጉሥ የሚኖርበትን ያህል'

በጋለሞታ ዘፈን እንደሚሆን እንዲሁ ይሆናል

ይህ የጢሮስ ሰዎች ጋለሞታ እንደነበሩ አይነት መስሎ ይናገራል፡፡ ታዋቂነቷን ያጣች ጋለሞታ የቀድሞ ፍቅረኞቿን እንደገና ለማግኘት በየመንገዱ እንደምተዘፍን፣ የጢሮስ ሰዎች እንደገና ባላጸጎችና ኃያላን ይሆኑ ዘንድ ንግዱን ለማስቀጠል ከሌሎች ሕዝቦች ወደ እነርሱ የሚመለሱ ሰዎችን ለማግኘት የጢሮስ ሰዎች ጥረት ያደርጋሉ፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ትታወሺ ዘንድ

ይህ በአደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ሰዎች ያስታውሱሽ ዘንድ' ወይም "ሰዎች ወደ አንቺ ይመለሱ ዘንድ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)