am_tn/isa/23/08.md

2.2 KiB

በጢሮስ ላይ ይህን ያቀደ ማነው? … የምድር

ኢሳይያስ በጢሮስ ላይ ለመሳለቅ ይህን ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ "ይህን' የሚለው ቃል ኢሳይያስ በ23፡1-7 የገለጸውን ጢሮስን ለማጥፋት የተዘጋጀውን የእግዚአብሔር እቅድ ያመለክታል፡፡ እንዲሁም ጢሮስ የሚለው በጢሮስ የሚነሩትን ሰዎች ያመለክታል፡፡ ይህ አሳብ ገላጭ ጥያቄ በአሳብ ገላጭ አረፍተ ነገርነት ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "የጢሮስን ሰዎች ለማጥፋት ያቀደው እግዚአብሔር ነበር … የምድር' (አሳብ ገላጭ ጥያቄና ምትክ ስም ተመልከት)

ዘውዶችን ሰጪ

በዚህ ስፍራ "ዘውድ' የሚለው አንድ ሰው እንደ ገዢ በሕዝብ ላይ ያለውን ሥልጣን ያመለክታል፡፡ አት፡- "በሌሎች ላይ እንዲገዙ ለሰዎች ሥልጣንን የሚሰጥ' (ምትክ ስም ተመልከት)

ነጋዴዎቿ ልዑላን ናቸው

ወደ ሌሎች አገሮች ሲሄዱ ምን ያህል ሥልጣን እንዳላቸው በአጽንዖት ለመናገር ነጋዴዎቹ ከልዑላን ጋር ተነጻጽረዋል፡፡ አት፡- "ነጋዴዎቿ እንደ ልዑላን ናቸው' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ነጋዴዎቿ … የምድር ክቡራን ናቸው

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "የምድር ሕዝቦች እጅግ ከፍተኛ ክብር የሚሰጡአቸው ነጋዴዎቿ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ክብሯን ሁሉና ትዕቢቷን ለማዋረድ

"በገዛ ራሳቸው ክብር ስለሚመኩ እነርሱን ለማዋረድ'

ትዕቢቷ … ክብሯ … ክቡራኖቿ

በዚህ ስፍራ እርሷ የሚለው በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች የምትወክለውን የጢሮስን ከተማ ያመለክታል፡፡ አት፡- "ትዕቢታቸው … ክብራቸው … ክቡራኖቻቸው' (ምትክ ስም ተመልከት)