am_tn/isa/22/25.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህ ያለፈው ቁጥር ቀጣይ ምስላዊ ገለጻ ነው፡፡ (ኢሳይያስ 22፥23-24 ይመ.)

በዚያ ቀን

‹‹በዚያ ጊዜ››

ይህ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ቃል ነው

የተናገረውን እርግጠኝነት ለማመልከት ያህዌ ስሙን በመጥራት ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ኢሳይያስ 14፥22 ላይ እንደ ተረጐምህ ተርጉመው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይህ የሰራዊት ጌታ ያህዌ የተናገረው ነው›› ወይም፣ ‹‹ይህ የሰራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው››

በአስተማማኝ ስፍራ የተተከለ ካስማ… ተሰብሮ ይወድቃል

ያህዌ ሳምናስ ቤተ መንግሥት ውስጥ የነበረውን ሥልጣን እንዲያጣ ማድረጉ ሳምናስ ግድግዳ ላይ እንዳለና ተሰብሮ እንደሚወድቅ ካስማ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ይህ አጽንዖት የሚሰጠው ሳምናስ ሥልጣኑ አስተማማኝ እንደ ሆነ ማሰቡንና እግዚአብሔር ግን ያንን የሚያስወግድ መሆኑን ነው፡፡

የተሸከመውም ሸክም ወድቆ ይከሰከሳል

እዚህ ላይ፣ ‹‹ሸክም›› የሳምናስን ኀይልና ሥልጣን ይወክላል፡፡ ሳምናስን የሚወክለው ካስማ ላይ በተሰቀለ ነገር ተመስሎአል፡፡ ያህዌ ሳምናስ ኀይልና ሥልጣኑን እንዲያጣ ማድረጉ፣ ካስማው ላይ ተንጠልጥሎ የነበረው ዕቃ ወድቆ መስበር ማለት እንደሆነ ተነግሯል፡፡