am_tn/isa/22/20.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ለሳምናስ የእግዚአብሔርን መልእክት መናገሩን ቀጥሏል፡፡

በዚያ ቀን ይመጣል

‹‹ይህ በዚያ ቀን ይሆናል››

አልያቂም… ኬልቅያስ

እነዚህ የሰው ስሞች ናቸው

መጐናጸፊያህን አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህንም አስታጥቀዋለሁ

ያህዌ ኤልያቂም ቤተ መንግሥት ውስጥ የሳምናስን ቦታ እንዲወስድ ማድረጉ ቤተ መንግሥት ውስጥ ሥልጣኑን የሚወክለውን የሳምናስን ልብስ ለአልያቄም ማልበስ እንደሆነ ተናግሯል፡፡

መጐናጸፊያህን… መታጠቂያህን

እዚህ ላይ፣ መጐናጸፊያና መታጠቂያ ቤተ መንግሥት ውስጥ ሥልጣንን ያመለክታሉ፡፡

መታጠቂያ

ይህ ሰዎች ወገባቸው ላይ ወይም ደረታቸው ላይ የሚያደርጉት የልብስ ዐይነት ነው፡፡ ኢሳይያስ 3፥20 ላይ እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

በእጁ

‹‹እጅ›› ኀይልና ቁጥጥርን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለእርሱ››

እርሱ አባት ይሆናል

አልያቄም ለይሁዳ ሕዝብ ማሰቡና መጠንቀቁ እርሱ አባታቸው እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ እንደ አባት ይሆናል››

ለይሁዳ ቤት

እዚህ ላይ፣ ‹‹ቤት›› ሕዝብን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለይሁዳ ሕዝብ››

የዳዊትን ቤት መክፈቻ በትከሻው ላይ አደርጋለሁ… ማንም አይከፍትም

እዚህ ላይ ‹‹ቁልፍ›› የሚወክለው ሥልጣንን ነው፡፡ ማንም የማይከፍተው ወይም ማንም የማይዘጋው የቤተ መንግሥቱ መክፈቻ እንዳለው ሁሉ ይህም ኤልያቂም ማንም የማይቃወመው ሥልጣን እንዳለው ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ቤተ መንግሥቱ ውስጥ በሚሠሩት ላይ ኀላፊነት እሰጠዋለሁ፤ የሚያደርገውን ውሳኔ ማንም መቃወም አይችልም፡፡››