am_tn/isa/22/17.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ለሳምናስ የእግዚአብሔርን መልእክት መናገር ቀጥሏል፡፡

አዙሮ አዙሮ እንደ ኳስ አጡዞ ወደ ሰፊ አገር ይወነጭፍሃል

የጠላት ወታደሮች መጥተው ሳምናስን በምርኮ ወደ ሌላ አገር መውሰዳቸው ያህዌ እንደ ኳስ ወደ ሌላ አገር እርሱን መወርወር ተደርጐ ተነግሯል፡፡

ለጌታህ ቤት ማፈሪያ ትሆናለህ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ቤት›› ንጉሡ ቤተ መንግሥት ውስጥ የሚሠሩ ሰዎችን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጌታህ ቤተ መንግሥት ውስጥ ላሉት ሁሉ እፍረት ታመጣለህ››

ከማእረግህ አወርድሃለሁ፤ ከኀላፊነትህም ትባረራለህ ወደ ታች ትጐተታለህ

ያህዌ ሳምናስን ቤተ መንግሥት ውስጥ እንዳይሠራ ማድረጉ ያህዌ እርሱን ወደ መሬት መወርወሩ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ወደ ታች ትጐተታለህ

ይህን በሌላ መልኩ መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከክብር ቦታህ ወደ ታች አወርድሃለሁ››