am_tn/isa/22/12.md

1.5 KiB

የሰራዊት ጌታ ያህዌ

ኢሳይያስ 1፥9 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

ጠጉራችሁን እንድትላጩ

ይህ የልቅሶና የንስሐ ምልክት ነው፡፡

እንብላ እንጠጣ፤ ነገ እንሞታለንና

እዚህ ላይ፣ ‹‹እንብላ እንጠጣ›› ድግስ ማድረግን፣ አለቅጥ መብላትንና ወይን ጠጅ መጠጣትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኛም የምንፈልገውን ያህል እየበላንና እየጠጣን አሁን ደስ ይበለን፤ ምክንያቱም በቅርቡ እንሞታለንና››

ይህን በጆሮዬ የገለጠ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ነው

‹‹ጆሮ›› የኢሳይያስን ሁለንተና ይወክላል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይህን የገለጠልኝ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ነው››

ይህ ኀጢአት እስክትሞቱ ድረስ አይሰረይላችሁም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሌላው ቀርቶ በምትሞቱበት ቀን እንኳ ቢሆን፣ ያደረጋችሁትን ኀጢአት ይቅር አልላችሁም››

ስትሞቱ እንኳ

ይህም ማለት፣ 1) ከሞቱ በኃላ እንኳ ያህዌ ይቅር አይላቸውም ወይም 2) እስኪሞቱ ድረስ ያህዌ ይቅር አይላቸውም፡፡