am_tn/isa/22/08.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ሰራዊት የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ስለሚያጠቃበት ወደ ፊት ስላለው ጊዜ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ የኀላፊ ጊዜ የወደ ፊት ጊዜ ተደርጐ መተርጐም ይችላል፡፡

የይሁዳን መከላከያ ወሰደ

‹‹መከላከያ›› የሚለውን የነገር ስም ግሥ አድርጐ መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ የይሁዳን ሕዝብ የከለለውን ማንኛውንም ነገር ወስዷል››

በዚያ ቀን የጦር መሣሪያ ተመለከትህ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ተመለከትህ›› የሚለው በአንዳች ነገር መተማመን ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለራስህ ለመከላከል መሣሪያ ታገኛለህ››

የዱር ቤተ መንግሥት

ይህ የጦር መሣሪያ የሚያከማቹበት በኢየሩሳሌም የነበረው ቤተ መቅደስ አካል የነበረ ቤት ነው፡፡

በታችኛው ኩሬ ውሃ አጠራቀምህ

ጠላቶች ከተማቸውን ሲከቡ የሚጠጡት በቂ ውሃ እንዲያገኙ ሕዝቡ ውሃ ያጠራቅማሉ፡፡