am_tn/isa/22/05.md

1.9 KiB

ቀን አለው

‹‹ጊዜ ይኖረዋል››

የመጯጯህ፣ የመረገጥ፣ ከሰራዊት ጌታ ያህዌ ዘንድ የሆነ ግራ የመጋባት

‹‹የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሽብር፣ መረገጥና ግራ መጋባት ሲያደርግ››

መረገጥ

ይህም ማለት፣ 1) የሚገሠግሡ ወታደሮችን ሊያመለክት ይችላል ወይም 2) ከሽብር የተነሣ ወዴት እንደሚሄዱ እንኳ ሳያውቁ የሚሮጡ ሰዎችን ሊያመለክት ይችላል፡፡

በራእይ ሸለቆ ውስጥ

ይህ የሚያመለክተው ኢየሩሳሌምን ነው፡፡ ኢሳይያስ 22፥1 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

ወደ ተራሮች የሚጮኹ ሰዎች

ይህም ማለት፣ 1) ‹‹ተራሮች ላይ ያሉ ሰዎች ጩኸታቸውን ይሰማሉ›› ወይም 2) ‹‹የሕዝቡ ጩኸት ከተራሮች ያስተጋባል››

ኤላም የፍላጻ ሰገባ ወሰደች

ሰገባ ፍላጻዎች የሚያዙበት ኮሮጆ ሲሆን፣ የቀስተኛውን መሣሪያ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የኤላም ሰዎች ቀስትና ፍላጻዎቻቸውን ወሰዱ››

ቂር ጋሻዋን አነገበች

እዚህ ላይ፣ ‹‹ቂር›› ወታደሮቹን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የቂር ወታደሮች ጋሻዎቻቸውን ከመያዣዎቻቸው ያወጣሉ››

ቂር

ቂር ሜዶን ውስጥ ያለች ከተማ ናት፡፡

መልካሞቹ ሸለቆዎቻችሁ

እዚያ ላይ፣ ‹‹የእናንተ›› የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ይወክላል፡፡ ኢሳይያስ ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዱ ስለሆነ ራሱንም ይጨምራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መልካም ሸለቆዎቻችን››