am_tn/isa/21/13.md

1.6 KiB

ንግር

‹‹ይህ ያህዌ የተናገረው ነው›› ወይም፣ ‹‹ይህ የያህዌ መልእክት ነው››

ስለ ዐረቢያ

ዐረቢያ የዐረቢያ ሕዝብን ይመለከታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለ ዐረቢያ ሕዝብ››

በዐረቢያ ምድረ በዳ

ዐረቢያ ደን የላትም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከዐረቢያ መንገድ በጣም ርቆ›› ወይም፣ ‹‹ከዐረቢያ ቆጥቋጦዎች ውጪ››

ሲራራ ነጋዴዎች

በአንድነት የሚጓዙ ሰዎች

የድዳን ሰዎች

እነዚህ በዐረቢያ የሚኖሩ ሰዎች ናቸው፡፡

የቴማ ምድር

ይህ አረቢያ ውስጥ ያለ ከተማ ስም ነው፡፡

ስደተኞች

ስደተኛ ጠላት እንዳይይዘው የሸሸ ሰው ነው፡፡ ኢሳይያስ 15፥5 ላይ እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

ከእንጀራ ጋር

‹‹እንጀራ›› በአጠቃላይ ምግብን ያመለክታል፡፡

ከሰይፍ፣ ከተመዘዘ ሰይፍ፣ ከተደገነ ቀስት

እዚህ ላይ፣ ‹‹ሰይፍ›› እና፣ ‹‹ቀስት›› የቴማን ነዋሪዎችን የሚያጠቁ ወታደሮችን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሰይፍና በቀስት ከሚያጠቋቸው ጠላቶቻቸው››

ከጦርነት ሸክም

በጦርነቱ ጊዜ የሚደርስባቸው ሽብርና መከራ ሕዝቡ ላይ እንደ ተጫነ ከባድ ሸክም ተመስሎአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከጦርነት ሽብር››