am_tn/isa/21/11.md

1.1 KiB

ንግር

‹‹ይህ ያህዌ የተናገረው ነው›› ወይም፣ ‹‹ይህ የያህዌ መልእክት ነው››

ስለ ዱማ

ይህ የኤዶም ሌላ ስም ነው፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹ዱማ›› እዚያ የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለ ዱማ ሕዝብ›› ወይም፣ ‹‹ስለ ኤዶም ሕዝብ››

እንዲህ ሲል ጠራኝ

‹‹እኔን›› የሚለው ኢሳይያስን ነው፡፡

ሴይር

ይህ ከኤዶም በስተ ምዕራብ ያለ ተራራ ስም ነው፡፡

ጠባቂ ሆይ፣ ሊነጋ ምን ያህል ቀረው? ጠባቂ ሆይ፣ ሊነጋ ምን ያህል ቀረው?

ይህ የተደጋገመው ጥያቄውን ያቀረበው ሰው ምን ያህል እንደ ተጨነቀና ግራ እንደ ተጋባ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡

መጠየቅ ከፈለግህ ጠይቅ፣ ደግሞም ተመልሰህ ና

‹‹ማወቅ የፈለግኸውን አሁን ጠይቀኝ፤ ደግሞም በኃላ ተመልሰህ ናና ጠይቀኝ››