am_tn/isa/21/03.md

1.0 KiB

ወገቤ በስቃይ ተሞላ

ኢሳይያስ ያየው ራእይ በጣም አስጨናቂ ስለ ነበር አካላዊ ሕመም አሳድሮበት ነበር፡፡ እዚህ ላይ ስቃዩና ሕመሙ ምኑ ላይ እንደነበር ይናገራል፡፡

በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ያዘኝ

ኢሳይያስ ሕመሙን ምጥ ከያዛት ሴት ሕመም ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ይህም ሕመሙ ምን ያህል ከባድ እንደ ነበር ያመለክታል፡፡

የሰማሁትን ነገር አጐበጠኝ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሰማሁት ነገር በሕመም አጐበጠኝ››

ባየሁት ነገር ተሸበርሁ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያየሁት ነገር በጣም አሸበረኝ››

ልቤ መታ፤ ፍርሃት አንቀጠቀጠኝ

‹‹ልቤ በፍጥነት መታ፤ እኔም ተንቀጠቀጥሁ››