am_tn/isa/21/01.md

2.8 KiB

ንግር

‹‹ይህ ያህዌ የተናገረው ነው›› ወይም፣ ‹‹ይህ የያህዌ መልእክት ነው››

ባሕሩ ዳር ስላለው ምድረ በዳ

ይህ እንደ ምድረ በዳ አድርጐ የተነገረ ቃል የሚያመለክተው የባቢሎንን ሕዝብ ነው፤ ምንም እንኳ እግዚአብሔር ገና ምድረ በዳ ባያደርጋትም አሁን እንደሆነች አድርጐ ይናገራል፤ ይህም የሚያመለክተው በእርግጥ ምድረ በዳ እንደምትሆን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በቅርቡ ምድረ በዳ በምትሆን ምድር ለሚኖር ሕዝብ››

እየጠራረገ ከኔጌቭ እንደሚመጣ ዐውሎ ነፋስ

ሕዝቡን ለማጥቃት የሚመጣውን ሰራዊት እግዚአብሔር ከብርቱ ነፋስ ጋር አመሳስሎታል፡፡ ፈጣንና ኅይለኛ ሰራዊት ነው፡፡

ከምድረ በዳ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ምድረ በዳ›› የይሁዳን ምድረ በዳ ነው የሚያመለክተው፡፡

ከአሸባሪ ምድር

ሰራዊቱ የሚመጣው ታላቅ ፍርሃት ከሚያደርስ ሕዝብ ነው፡፡

የሚያስጨንቅ ራእይ አየሁ

ይህን በሌላ መልኩ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ የሚያስጨንቅ ራእይ አሳየኝ››

ከሐዲ ክሕደቱን ያደርጋል

‹‹የሚያሳስቱ ያሳስታሉ››

አጥፊም ያጠፋል

‹‹የሚያጠፉ ይጠፋሉ››

ወደ ላይ ወጥታችሁ አጥቁ፣ ኤላም፣ መክበብ፣ ሜዶን

ለኢሳይያስ በተሰጠው ራእይ እግዚአብሔር እርሱን እንደሚሰሙ አድርጐ ለኤላምና ለሜዶን ሰራዊት ይናገራል፡፡

ወደ ላይ ወጥታችሁ አጥቁ፤ ኤላም፣ መክበብ፣ ሜዶን

የሚያጠቁት ባቢሎናውያንን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወደ ላይ ወጥታችሁ ባቢሎናውያንን አጥቁ፤ እናንት የኤላም ሰራዊት ሄዳችሁ›› ባቢሎናውያንን ክበቡ፤ እናንት የሜዶን ሰራዊት››

ኤላም… ሜዶን

እዚህ ላይ፣ ‹‹ኤላም›› እና፣ ‹‹ሜዶን›› ከእነዚህ አገሮች የመጡ ሰራዊት ያመለክታል፡፡

እርሷ ያደረሰችውን ስቃይ ሁሉ አስቀራለሁ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እርሷ›› በባቢሎናውያን ምክንያት መከራ የደረሰባቸውን ሕዝብ ሁሉ ይወክላል፡፡ የኤላምና የሜዶንን ሰራዊት ልኮ ባቢሎናውያንን ሲደመሰስ ያህዌ ስቃያቸውን ሁሉ ያስቀራል፡፡