am_tn/isa/20/05.md

1.1 KiB

ይደነግጣሉ ይዋረዳሉ

‹‹ይፈራሉ፤ እፍረት ይይዛቸዋል››

ተስፋቸው ከሆነው ኩሽ፣ ክብራቸው ከሆነው ግብፅ የተነሣ

ተስፋና ክብር በእነዚህ አገሮች ወታደራዊ ኀይል መተማመናቸውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በኩሽና በግብፅ ሰራዊት ኀይል ከመተማመናቸው የተነሣ››

በእነዚህ ባሕር ዳርቻዎች የሚኖሩ

ሜዲትራንያን ባሕር ዳርቻ የሚኖሩ ሕዝቦች

እንዲድኑን የሸሸንባቸው

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያድኑናል በማለት ሸሽተን የነበርንባቸው አገሮች››

ታዲያ፣ አሁን እንዴት እናመልጣለን?

ጸሐፊው ይህን ጥያቄ ያነሣው ሁኔታው ምን ያህል ተስፋ የሌለው መሆኑን አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አሁን ምንም ማምለጫ የለንም››