am_tn/isa/17/12.md

1.7 KiB

የብዙ ሕዝብ ጩኸት፤ እንደ ባሕር ሞገድ ያለ ጩኸት

ጩኸት በጣም ከፍ ያለ ድምፅ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ባሕር ሞገድ በጣም ከፍ ያለ የብዙ ሰዎች ድምፅ››

እንደ ውሃ ሙላት የተጣደፈ የሕዝቦች ሩጫ

የጠላት ሰራዊት ማንም የማያስቆመው ታላቅ ኀይል ይመስላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሕዝቡ እንደ ውሃ ሙላት እየተጣደፉ ይመጣሉ››

የሕዝቦች ጥድፊያ

‹‹ሕዝቦች›› የሚለው ቃል የእነዚህ አገሮችን ሰራዊት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጠላት ሰራዊት ጥድፊያ››

በዐውሎ ነፋስ ፊት ተራራ ላይ እንዳለ ገለባ… በማዕበል ፊት እንደሚበተን አረም

እነዚህ ሁለት ሐረጐች ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ የጠላት ሰራዊት በጣም ኀይለኛ ይመስላል፤ እግዚአብሔር ግን በቀላሉ ያስቆማቸዋል ያባርራቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ነፋስ እንደሚያበንነው ተራራ ላይ እንዳለ ገለባ… ማዕበል ሲመጣ በንኖ እንደሚጠፋ አረም››

የ… ዕድል ፈንታ

እነርሱ ላይ የደረሰው በውርስ እንዳገኙት ዕድል ፈንታ ተመስሎአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በ… የሚደርሰው ይኸው ነው››

የዘረፉን… የበዘበዙን

‹‹እኛን›› የሚለው ኢሳይያስንና የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታል፡፡