am_tn/isa/17/10.md

997 B

አንተ ረስተሃልና

‹‹አንተ›› የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው፡፡ ‹‹ረስተሃል›› የሚለው ቃል እግዚአብሔርን አያስታውሱም ማለት አይደለም፡፡ እየታዘዙለት አይደለም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አልታዘዝህምና››

አዳኝ አምላክህን

‹‹የሚያድንህን አምላክ››

የብርታትህን ዐለት ችላ ብለሃል

እዚህ ላይ እግዚአብሔርን ከጠላቶቻቸው ለማምለጥ ወይም ከጀርባው ለመደበቅ ሰዎች ከሚወጡበት ትልቅ ዐለት ጋር አመሳስሎታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ መከታ ዐለት የሆነልህን ችላ ብለሃል›› ወይም፣ ‹‹የከለለህን ችላ ብለሃል፡፡

መከር ይበላሻል

‹‹የምትሰበሰቡት ብዙ ፍሬ አይኖራችሁም››